Saturday, November 21, 2015

እርቃኑ የወጣ ያደረ በሽታ!



በአንድ አገር የሁሉም ነገር መሰረት መልካም አስተዳደር ሲኖር ነው ኣንድን ስርአት እየመራሁት ነኝ በሚለው ህዝብ ዉስጥ እዉነተኛና መልካም ኣስተዳደር መዘርጋት ካልቻለ ሌላ ጥሩ ነገር ሊሰራ ይችላል ብለህ ኣይጠበቅም፣ ምክንያቱ ሁሉም ነገር በአስተዳደር ዙርያ ስለ ሚጨረሽ።

     በአገራችን ዋነኛው ህመም ሁኖ የቆየና ያለ የመልካም አስተዳደር በሽታ ነው፣ ይህ በሽታ የስርአቱ የስልጣን እድሜ ያስቆጠረ ቢሆንም ስርአቱ ግን የመልካም አስተዳደር ችግር የለኝም እያለ በኣስተዳደሩ ብልሹ ኣሰራር ምክንያት የተነሳ ብህዝባችን ላይ እየተፈፀመ የቆየው በደል ሲክደው ቆይተዋል።

ህዝብችን ደግሞ በተቃራኒ በመልካም ኣስተዳደር እጥረት በክልል ዘን ወረዳና ቀበሌ ኣስተዳዳሪዎች ከባድ ችግር እውየወረደው እንደሚገኝ በስርኣቱ ላይ እየተቃወመ እና ኣቤቱታዉን እያሰማ እንደቆየ ስርኣቱም ቢሆን ሊክደው የማይችል የተረጋገጠ ሃቅ ነው፣ ህዝባችን መልካም ኣስተዳደር ከመባል ኣልፎ የጥፋት ኣስተዳደር ነው ለማለትም በቅቷዋል።

በስልጣን ላይ የሚገኝ ስርኣት በመደናገር እና በማካድ ተግባር የታወቀ ስለ ሆነ በአገራችን ተከስተው የሚገኙ የዴሞክራሲና የምልካም ኣስተዳደር  እጥረት የወለደባቸው የህዝባችን ሰብኣዊ መብት የሚጥሱ ኢ-ዴሞክራስያዊ የሆኑ ፍፃሜዎች ሲክዳቸው ቆይተዋል።

  እዉነት ለግዜው ሊደበቅ ይችል ይሆናል እንጂ። ከነ ኣካቴው ሊደበቅ   የሚቻል ኣይደለም፣ ስለ ሆነ ለህዝባችን በጉርረው ኣንቆ በመያዝ የካድሬዎች እና ተላላኪዎች መጠን የሌለው የገቢ ምንጭ ሁኖ የቆየ የመልካም ኣስተዳደር እጥረት ዛሬ እርቃኑ ሊወጣ ችሏዋል።

 ሙሱና እና ብልሹዉ ኣሰራር የወለደው የመልካም ኣስተዳደር  እጥረት ከጫፍ እስከ ጫፍ የኣገራችን ክፍል መሰረት ኣንጥፎ ስርኣቱ ሊደብቀው በማይችልበት መድረክ ሰለ ደረሰ  የኢህኣዴግ ስርኣት ግን  ለህዝብ እና ለኣገር የሚቆረቆር። ሙስና የሚጠላ መስሎ በመቅረብ በኣገር ደረጃ ጥናት ለመካየድ ጀምሬያለህ ይለናል።

በተካሄደው ጥናት መሰረት ከሌሎች ክልሎች በላይ እንደተጠቀመች ህዝብዋ ዴሞክራሲ እንዳገኘ ልማት ያረጋገጠች እየተባለች ሲነገርባት የቆየ ትግራይ ክልል ሙሱና በሰፋ መልኩ ከታየባቸው  ክልሎች በቅድምያ እንድትጠራ ችላለች፣ ይህ ደግሞ የትግራይ ህዝብ የስርኣቱ ዋና ተጠቃሚ ነው ለሚል የተዛባ ኣስተያየት የሚያርም ነጥብ ነው።

 በኣሁኑ ግዜ በኣገራችን በቂ ገንዘብ ካለህ ለፍትህ ፤ለዳኛ፤ ለባለ ስልጣን፤ ለፖሊስና ለሌሎች  የመንግስት ኣካላት በኪስህ ዉስጥ ይዘሃቸው ለመዞር የምትችልበት ሰፊ እድል ኣለ፣ ኣጠር ባለ ኣገላለፅ ለህግ በገንዘብ መግዛት ይቻላል ማለት ነው። ይህ ደግሞ ለግል ጥቅማቸው ባደሩ ከፍተኛ የኢህኣዴግ መሪዎች የፈጠሩት መርዛም ተግባር ነው።

    በአንድ አገር  ከባድ ወንጀል ፈፅመዋል  ተብሎ እንዲታሰር የተፈረደ  ሰው በገንዘቡ ነፃ የሚልቀቅበት ፍትህ እና እዉነት  ብገንዘብ ሃይል በሚጠፋበት በኣሁኑ ግዜ በኣጠቅላይ መንግስታዊ ኣገልግሎት ለማግኘት የሄደ ህዝብ ብእግርህ ነው በእጅህ የመጣህ ተብሎ በሚጠየቅበት አገር መልካም ኣስተዳደር የለም ከማለት መንግስት የለም ማለት ይቀላል።

 የህወሓት ኢህኣዴግ ስርኣት ያ ሁሉ ጉድ ሲደብቀው እና ሲክደው ከቆየ በኋላ ዛሬ ከቁጥጥሩ ዉጭ ሁኖ ሊፈነዳ ሲል የመልካም ኣስተዳደር ችግር ለመቅረፍ በቆራጥነት ተነሳስቻሎህ ብሎ መንቀሳቀስ መጀመሩ "ጅብ ከሄደ  ዉሻ ጮሀ " ከመሆን ኣልፎ ሌላ ትርጉም  ሊሰጠው ኣይችልም።
 
ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የመንግስት ኣስተዳደር ኣካላት የህግ ኣስከባሪዎች እና ዳኞች ፖሊስ እና ድህንነት እንድሁም ፀረ ሙስና ኮምሽን የሚባሉ ተቓማት በሙሱና የበሰበሱና ጥሩን ኑሮ የለመዱ ስለሆኑ በኣገራችን መሰረታዊ የስርኣት ለዉጥ ሳይደረግ ሙሱና ሊወገድ ከቶ ኣይችልም።

በኣሁኑ ግዜ እየተደረገ ያለው ለመልካም ኣስተዳደር የሚያደናቅፍ መሰናክሎች  እናወግዳለን የሚል የይስሙላ እንቅስቃሴ  የህዝብ ስሜት ለማወቅ እየተጠቀሙበት የሚገኙ የተደበቀ ኣጀንዳ ከመሆን ኣልፎ የኢህኣዴግ መሪዎች ለየብቻቸው ሁኖው የህዝብ ችግር በማየት የሚፈታ ድፍረት የላቸዉም።

በሚያጋጥሙህ ስህተቶች ልትገመገምና ልትማርባቸው ቆራጥነት ይጠይቃል ይሁን እንጂ የወያኔ ኢህኣዴግ መሪዎች ግን ተሳስተናል በማለት የማይቀደሙ ቢሆኑም ስህተታቸው በማረም እና በመስተካከል ግን የተዘጉ ናቸው፣ ስለ ሆነም ለዚህ እራቆቱ ወጥቶ የሚገኝ የመልካም ኣስተዳደር እጥረት ይፈታል ብለህ መጠበቅ የስርኣቱ ባህሪ ካለ ማወቅ የሚነሳ የዋህነት ነው።