Thursday, February 2, 2017

በኢሮብ ወረዳ ደውሃን ከተማ ኣከባቢ የሚኖሩ ወገኖቻችን በከባድ የንፁህ መጠጥ ውሃ እጥረት እየተሳቃዩ መሆናቸውን ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ኣስታወቀ።



   የደውሃን ከተማ ህዝብ ኣጋጥሞት ባለ ንፁህ የመጠጥ ውሃ እጥረት ምክንያት ፅዳቱ ያልተጠበቀ ውሃ ለመጠጥ እና ለምግብ ማብሰያ እየተጠቀሙ በመሆናቸው ለተለያዩ የውኃ ወለድ በሽታዎች እየተጋለጡ እንደሚገኙ  መረጃው የገለፀ ሲሆን፣ በኣቅራብያቸው በተመጣጣኝ  የህክምና ክፍያ ሊያገኙ ባለመቻላቸው ደግሞ ተጨማሪ ችግር ሆነባቸው እንዳለ ነዋሪዎቹ ኣስረድተዋል።
   በወረዳዋ ውስጥ ለሁሉም ቀበሌዎች የሚያገናኝ መንገድ ባለመኖሩ  ደግሞ ነዋሪዎቹ ህመምተኛ ተሸክመው ወደ ህክምና ለመማላለስ ተቸግረው እንዳሉ ታውቋል። ህ.ወ.ሃ.ት ትግራይን በመንገድ የጠፍር አልጋ አደርጋታለሁ ሲል   የኖረ ቢሆንም መንገድ ተስፋፍቶ የጠፍር አልጋ ሊመስል ይቅርና           ህመምተኞችን ሊረዱ የሚችሉ የኣምቡላንስ መንገድ እንኳን ሊሰራ ያልቻለ በመሆኑ ህዝብ ምሬቱን እያሰማ መሆኑ ጨምረው ኣስረድተዋል።
   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በደውሃን ከተማ እየታየ ያለ የንፁህ ውሃ እጥረትና የመንገድ ችግር በሙሉ የትግራይ ወረዳዎች በተደጋጋሚ ህዝብ የሚያነሳቸው ችግር ሲሆኑ ይሁን እና በመንግስት ትኩረት ተደርጎባቸው  መፍትሔ  ያላገኙ ችግሮች ሁነው እየቀጠሉ  መሆናቸው ተገልጿል፣



No comments:

Post a Comment